ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

EED ሰኔ 23/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የውጪ ንግድና የተኪ ምርት የድጋፍና የክትትል የአሠራር ስርዓት ላይ ከስራ አመራር አባላትና ሌሎች መካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በመድረኩ የድጋፍና የክትትል የአሠራር ስርዓቱ ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን ዓላማውም በተኪና ወጪ ምርት ማምረት ላይ ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በመስጠት ምርትና ምርታማነታቸውን ማሳደግና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነታውን ማረጋገጥ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በመድረኩ እንደገለጹት አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍና የማምረት አቅማቸውን በማሳደግ በተኪና ወጪ ምርት ላይ እንዲሰማሩ ለማስቻል በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ተኪና ወጪ ምርት ላይ የተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በተመለከተ የጠራ መረጃ መያዝ ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ በኢንተርፕራይዝ ደረጃ እቅድ ማቀድና የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ደረጃ በደረጃ መፍታት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ በበኩላቸው የውጪ ንግድና የተኪ ምርት የድጋፍና የክትትል የአሠራር ስርዓቱ ያለንን እውቀትና አቅም የምንፈትሽበትና ያለንበትን ደረጃ የምናውቅበት ይሆናል ብለዋል፡፡

የአሰራር ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ ኮሚቴ መቋቋሙን የገለጹት አቶ ጳውሎስ ይህም በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ ለመስራትና ወቅታዊነቱንና ጥራቱን የጠበቀ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር በማስቻል በዘርፉ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ያግዛል ብለዋል፡፡  

በመድረኩ የውጪ ንግድና የተኪ ምርት የድጋና የክትትል የአሰራር ስርዓቱን ለማዳበር የሚስችሉ ሀሳቦች ከተሳታፊዎች ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News