
የውይይቱ ተሳታፊዎች ኤልና ቴክስ የልብስ ስፌትና የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካን ጎብኝተዋል
EED ጥር 17/2018
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ በአርባ ምንጭ ከተማ ውይይት ማካሄዱ ይታወቃል::

የውይይቱ ተሳታፊዎች በከተማዋ የሚገኘውን በቅርቡ ስራ የጀመረውን ኤልና – ቴክስ የልብስ ስፌትና የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ጎብኝተዋል::

ኤልና – ቴክስ ጥራት ያላቸውን የደንብ ልብሶች፣ ቱታዎች፣ ጅንሶች፣ ሸሚዞች፣ ኮፊያዎችና ልዩ ልዩ አልባሳትን እያመረተ ለተጠቃሚዎች እያቀረበ የሚገኝ መሆኑን የገለፁት የድርጅቱ ባለቤት ወ/ሮ ዓለምነሽ አሉላ ለተለያዮ ለተቋማት የደንብ ልብሶችን በትዕዛዝ እያመረቱ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ወደ ስራ ለመግባት መነሻ የሆናቸው በሆቴል ስራ ሲቆዩ በአካባቢያቸው የስራ ወይም የደንብ ልብሶችን ለማግኘት እንደሚቸገሩና ይህንን ችግር ለመፍታት ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት በጋርመንት ዘርፍ ተመርቀው ለሚወጡ ለአካባቢው ተወላጅ የሴቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ኤልና – ቴክስ የልብስ ስፌት እና የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በ32 ሚሊየን ብር ካፒታል ወደስራ የገባ ሲሆን አሁን ላይ ለ61 ሴቶችና ለ13 ወንዶች በድምሩ ለ74 ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

ወ/ሮ ዓለምነሽ ሴቶችን መደገፍና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማበረታታት ሀገርን ማሳደግና መጥቀም በመሆኑ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በጉብኝቱ ኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የስራ-አመራር አባላት የዘርፉ የክልል ቢሮ ኃላፊዎችና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎችና የእቅድ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል::
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
#ለተጨማሪ_መረጃ