ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

“ፕሮጀክቱ ሲጀመር ከተቀመጡ ግቦች የተሻለ አፈፃፀም ተመዝግቧል!”

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

EED ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት የስራ ዘመን መጠናቅን አስመልክቶ የፕሮጀክት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚገልፅ ሪፖርት ቀረበ።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ ያመጣውን ትክክለኛ ተፅዕኖ ለማወቅ በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ባስጠናነው ጥናት መሠረት ፕሮጀክቱ ሲጀመር ከተቀመጡት ግቦች የተሻለ አፈፃፀም እንደተመዘገበ ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የካፒታል ዕቃ አከራይ ማህበራትን በማበራከትና አቅማቸውን በማጠናከር፤ የቴክኒካል ክህሎት ክፍተቶችን በመሙላት የምርት ጥራትን፣ ተወዳዳሪነትን እና ግብይትን ማሻሻል እንደቻለ፤ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ችግር ታሳቢ ያደረገና ልዩ ፈጠራ የታከለበት አዲስ የፋይናንስ አቅርቦት ስርዓት ለሀገራችን ማስተዋወቅ እንደቻለ ዶ/ር አለባቸው ገልፀዋል፡፡

ውጤቱ የተቋማት ተባብሮ የመስራት ድምር ውጤት መሆኑን ያመላከቱት ዶ/ር አለባቸው ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው የሊዝ ማሽን ኪራይ እና የስራ ማስኬጃ  ብድር እንዲሁም  የንግድ ስራ ልማት አገልግሎት /BDS/ ሳይቋረጥ አዲስ አማራጭ ፕሮጀክት በማዘጋጀት ስራውን ለማሳደግ ቅድሚያ ተሰጥቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በመድረኩ የአነስተኛና መካከለኛ ፋይናንስ ፕሮጀክስ ስራዎችን የሚዘክሩ የተለያየ ሀሳቦች ከመድረክ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል::

‎#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

‎ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News