የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት በተለይም በማኑፋክቸሪንግ በዘርፍ እድገት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ተግዳሮቶች ውስጥ ዋነኞቹ የካፒታል እጥረት፣ የቴክኖሎጂ እና የንግድ ስራ እውቀት ውሱንነት መሆኑን በመገንዘብ፤ በዋነኝነት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ተደራሽነት በማሳደግ ያለባቸውን የፋይናንስ እጥረት የመቅረፍና የንግድ ስራ አገልግሎት ስልጠናን የመስጠት ዋነኛ ዓላማን በመተለም የተነደፈ ነው፡፡
የፕሮጀክቱ ጽንሰ ሃሳብ የመነጨው እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ አቅርቦት ዙሪያ በዓለም ባንክ ከተደረገ ጥናት ሲሆን፣ ጥናቱ ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በማይክሮ ፋይናንስ በኩል የብድር አቅርቦት ተጠቃሚ እንደሆኑና፣ ትላልቅ ኢንተርፕራይዞች ደግሞ በባንኮች በኩል የብድር አቅርቦት የሚያገኙ መሆናቸውን ይጠቁማል፡፡ በዚሁ መሰረት በመካከል የሚገኙ በጥናቱ “Missing middle’’ የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አቅርቦት ችግር ያለባቸው መሆኑ ተለይቷል፡፡ በዚህ መነሻነት በጥናቱ እንደመፍትሄ ሃሳብ የቀረበው፤
ሀ. የማይክሮ ፋይናንሶችን አቅም በገንዘብና በስልጠና በማጎልበት የብድር አቅርቦት ስራቸውን ከፍተኛ የብድር ፍላጎት ወዳለበት ወደአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ትኩረት እንዲያደርጉ ማድረግ፣
ለ. የንግድ ባንኮችም የብድር አሰጣጥ ፖሊሲያቸውን በመፈተሽ ከትላልቅ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ድጋፍ በተጨማሪ ዝቅ ብለው አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የመደገፍ አካሄድ ላይ እንዲያተኩሩ፤ ይህም አሰራራቸው አሁን ያለውን የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር ፍላጎት መሰረት ያደረገ እንዲሆን ይጠቁማል፡፡
በዚህ ጥናት መነሻነት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ባንክ ባደረጉት ስምምነት እውን ተደረገ፡፡ በዚህም መሰረት የብድር ውል ስምምነቱ በኢትዮጵያ መንግስትና በዓለም ባንክ መካከል እ.አ.አ ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ተፈረመ፡፡
ፕሮጀክቱ አራት ኮምፖነንቶች ሲኖሩት አንደኛው በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚተገበር ሲሆን በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት /ኢኢል/ ስር የሚገኘው የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ የሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና አራተኛውን ክፍሎች አጠቃላይ የማስተባበር ሚናና ቀጥተኛ የትግበራን ኃላፊነት አለበት።
ይህ የፕሮጀክት አካል /Component/ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል የሚተገበር ሆኖ በዋና /Parent/ ፕሮጀክቱ 269 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን በተጨማሪ ፋይናንሱ 180 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተመድቦለታል፡፡ ይህ ገንዘብ ቀጥሎ በተገለጹት በሁለት መስኮት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርብ ይሆናል፡፡
ሀ) በቀጥታ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኩል ብቁ ለሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርብ የካፒታል ዕቃዎች የሊዝ ፋይናንስ፣
ለ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በንግድ ባንኮችና በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በኩል ብቁ ለሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚያቀርበው የስራ ማስኬጃ ብድር ነው።
የስራ ማስኬጃ ብድር በማቅረብ ተሳታፊ የሆኑ የፋይናንስ ተቋማት /Participating Financial Institutions/
ይህ የፕሮጀክት አካል /Component/ የሚተገበረው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና በፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ጥምረት ሲሆን ለዚህም 1.87 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በጀት ተይዞለታል፡፡ በዚህ ስር የሚሰሩ ስራዎች “ማዕከላዊ የኤሌክትሮኒክስ ዋስትና መመዝገቢያ መሳሪያ የመግዛት፣ የኪሳራ ምርመራ ቅኝትና የአበዳሪ/ተበዳሪ ህጋዊ አሰራር መዘርጋት” /Centralized electronic collateral registry/ ናቸው፡፡ በተጨማሪ ፋይናንሱ ተንቀሳቃሽ ንብረትን መሰረት ያደረገ የብድር ዋስትናና መረጃ ስርዓትን ለመዘርጋትና ለማጠናከር /Development of Movable Asset Based Lending/ 3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመድቦለታል፡፡
ይህ የፕሮጀክት አካል የሚተገበረው በፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ነው፡፡ በዋና ፕሮጀክቱ የተያዘለት በጀትም 2.26 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን ከተጨማሪ ፋይናንሱ 15 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተመድቦለታል፡፡ በዚህ የፕሮጀክት አካል /Component/ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን ይህም የንድፈ ሃሳባዊ ክህሎት (Soft skill) እና የቴክኒክና ሙያ ክህሎት (Technical skill) ስልጠናን የሚያጠቃልል ሲሆን ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በጋራ የሚሰራውን የኢ-ኮሜርስ እና የገበያ መረጃ ማዕከል ምስረታንም ይጨምራል፡፡
የሚከናወነው በፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ አማካኝነት ነው፡፡ ለዚህ የፕሮጀክት አካል /Component/ በዋና ፕሮጀክቱ 2.86 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተበጀተለት ሲሆን ከተጨማሪ ፋይናንሱ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተይዞለታል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ፣ ትርጉም ያለው የስራ እድል ለመፍጠር እና ለአገሪቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት ያለመ ነው ።