ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ለኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች በመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው

EED ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች በመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ላይ ስልጠና እየወሰዱ ነው። ስልጠናው ተቋሙ መንግስት ያስቀመጠውን የሪፎርም አቅጣጫ ወደ ተግባር ለመቀየር እያከናወነ ያለውን ጥረት የሚደግፍ ነው።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ ተቋሙ የሪፎርም ትግበራን ለማሳካት በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጸው ስልጠናው የአምራች ኢንዱስትሪ አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ስራዎችን እና የቀጣይ እቅዶችን በተመለከተ የሠራተኞችን ግንዛቤ ለማሳደግ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

በተቋሙ እየተተገበረ ያለው ሪፎርም ያለሰራተኞች ንቁ ተሳትፎ ስኬታማ መሆን አይችልም ያሉት አቶ ጳውሎስ ሰራተኞች ከስልጠናው በቂ እውቀት በመያዝ፣ ለሪፎርሙ ስኬት በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት­_እኛም_እንሸምት

ለተጨማሪ መረጃ

ቲክ ቶክ:  https://www.tiktok.com/@et.enterprisedevelopment

ድረ ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

ኤክስ፡ https://x.com/Ethio_EED

ሊንክድን፡ https://www.linkedin.com/in/ethiopian-enterprise-development-eed-57b784244/

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/eed_ethiopia/

News