ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

‹‹አምራች ኢንተርፕራይዞች በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ ራሳቸውን ማብቃት ይገባቸዋል!››

ወ/ሮ የመንዝወርቅ ግረፌ፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት አስተባባሪ

EED ግንቦት 20/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት በአዳማና ሀዋሳ የስልጠና ማዕከል 150 ለሚሆኑ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች ስልጠና መስጠት ጀመረ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት አስተባባሪ ወ/ሮ የመንዝወርቅ ግረፌ ባስተላለፉት መልዕክት አምራች ኢንተርፕራይዞች በአለምአቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ  መሆን እንዲችሉ ራሳቸውን ማብቃት እንደሚገባቸው አመላክተዋል፡፡

ለዚህም ይረዳ ዘንድ ስልጠናው በውጭ ገበያ ዝግጁነትና የገበያ ተደራሽነት (Export Readiness & Market Access)፤ በኤሌክትሮኒክስ ግብይት (Digital Marketing)፤ የቢዝነስ አስተዳደር ክህሎት (Business Management) እንዲሁም ኢንተርፕሪነርሽፕ ላይ በንድፈ-ሐሳብና በተግባር የተደገፈ  በመሆኑ ለአምራች ኢንተርፕራይዞች ጥሩ ልምድ እንደሚሆን አስረድተዋል።  

ፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም ለ2800 አምራች ኢንተርፕይራዞችና ለ270 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምህራን የንግድ ልማት ስራ አገልግሎት ዙሪያ ስኬታማ ስልጠና መሰጠቱን የገለፁት ወ/ሮ የመንዝወርቅ አጠቃላይ የፕሮጀክቱን ውጤታማነት ለመመዘን በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በተሰራ ጥናት ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው የሊዝ ማሽን ኪራይ እና የስራ ማስኬጃ  ብድር እንዲሁም  የንግድ ስራ ልማት አገልግሎት /BDS/ ውጤታማ እንደሆነ ማመላከቱን ገልፀዋል::

ስልጠናው በኮንሱል አማካሪ ድርጅት እየተሰጠ ሲሆን ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ፣  ከድሬዳዋ፣ ከሐረር፣ ከሲዳማ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች ተሳታፊ ሆነዋል::

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

News