ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

“አምራች ኢንዱስትሪዎችን ከተሞች ላይ ብቻ በማቀፍ ሀገራችን ልታድግ አትችልም!”

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮግራም በሁሉም የገጠር ወረዳዎች ቢያንስ አንድ አነስተኛ ወይም መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ለማቋቋም ይሰራል!

EED ጥር 27/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮግራምና አተገባበሩ ላይ ለክልልከተማ አስተዳደር አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተቋማት የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን አስተባባሪዎች ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮግራም በሁሉም የገጠር ወረዳዎች የአካባቢውን ፀጋ መሰረት ያደረገ ቢያንስ አንድ አነስተኛ ወይም መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ለማቋቋም እንደሚሰራ ስልጠናውን ያስጀመሩት የልማት መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ ገልፀዋል፡፡

የሀገር ውስጥ ሀብትና ጉልበትን የሚጠቀሙ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋም የገጠሩን ማህበረሰብ ከግብርና በተጨማሪ አዲስ የገቢ ምንጭ እንዲያገኝ በማድረግ ኑሮውን ማሻሻል ዋነኛ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን አላማ እንደሆነም አያይዘው ገልፀዋል፡፡

ኢንዱስትሪዎችን ከተሞች አካባቢ ብቻ በማቀፍ ሀገራችንን ማሳደግና ፍትሃዊ የሀብት ተጠቃሚነትን እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማረጋገጥ እንደማይቻል የገለፁት ዶ/ር አለባቸው ኢንዱስትሪን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለማስፋፋት አብላጫው ህዝብ በሚኖርበትና ግብዓት እንዲሁም ሰፊ የሰው ሃይል የሚኖርበትን የገጠር ወረዳዎች ድረስ በመውረድ የኢንዱስትሪውን መሰረት ማስፋፋት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

በመድረኩ  የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን አተገባበር እና የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ኢንቨስትመንት ማቋቋሚያና ማስፋፊያ ሰነድ ቀርበዋል፡፡

News