ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

“የሽግግርና የድጋፍ አፈጻጸም መመሪያው የኢትዮጵያን አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሠረት መጣልና የማስፋት ስራችንን ይደግፋል!”

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

EED ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ የዕድገት ደረጃ ሽግግርና ድጋፍ አፈጻጸም ረቂቅ መመርያ ላይ ከተለያዩ የፌደራልና የክልል ዘርፍ ማህበራትና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ የዕድገት ደረጃ ሽግግርና ድጋፍ አፈፃፀም ረቂቅ መመሪያው በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንዲዳብር መደረጉ ቅንጅታዊ አሰራርን እንደሚያጠናክር ገልፀዋል።

መመሪያው ፀድቆ ወደ መሬት ሲወርድ የብዙ ባለድርሻ አካላትን የተናጥል ጥረት ወደ አንድ ትብብርና ቅንጅት ማዕቀፍ በመቀየር ውጤታማ የአምራች ኢንተርፕራይዝ ዕድገት ደረጃ ሽግግርን ፍትሀዊ ማድረግ የሚችሉ የድጋፍ ማዕቀፎችንና የብቃት አምዶችን እንደያዘ ገልፀዋል።

እንደ ሀገር የአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፉን ለመምራት በተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ መሠረት የአምራች ኢንተርፕራይዞች የደረጃ  ሽግግር ስትራቴጂና መመሪያ መዘጋጀቱን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ መመሪያው የኢትዮጵያን አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሠረት የመጣልና የማስፋት ስራዎችን በተደራጀ ሁኔታ እንደሚደግፍ አመላክተዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com እናመሰግናለን::

News