
የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት የስራ ዘመን ተጠናቀቀ
EED ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም
ላለፉት 8 ዓመታት ለአነስተኛና መካከለኛ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የማሽን ሊዝ ፋይናንስ፣ የስራ ማስኬጃ ብድር፣ የንግድ ስራ ልማት አገልግሎትና መሰል አገልግሎቶችን ሲሰጥ የቆየው በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት በስኬት ተጠናቀቀ።

የፕሮጀክቱን በስኬት መጠናቀቅ ተከትሎ በተዘጋጀው የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ በነበረው ቆይታ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሊዝ ማሽን በኪራይ በማቅረብ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብለዋል።

በተጨማሪም የስራ ማስኬጃ ብድር በማቅረብና የንግድ ስራ ልማት አገልግሎት ስልጠና በማቅረብ የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ምክንያት እንደሆነ የገለፁት አቶ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በሰራቸው ተግባራት ላይ ሁሉ የፕሮጀክቱ አስተዋፅኦ እንደነበር ገልፀዋል።

በመጨረሻም የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ለዘርፉና ለተቋሙ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ዕውቅና በመስጠት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት
ለተጨማሪ መረጃ ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment
#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise
#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com