ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራሮች በወራቤ ከተማ ሶጃት ኢንዱስትሪ መንደር የችግኝ ተከላ አካሄዱ

EED ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራሮች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ሶጃት ኢንዱስትሪ መንደር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል::

ከችግኝ ተከላው ባሻገር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮቹ 1 ሺህ ሄክታር የሚሸፍነውን የሶጃት የኢንዱስትሪ መንደር ጎብኝተዋል፡፡

በዝግጅቱ የልማት መ/ቤቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የስልጤ ዞንና የወራቤ ከተማ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል::

የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ መጀመሩ ይታወሳል::

‎#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

‎ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News