ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

‹‹ሀገር-አቀፍ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስትራቴጂ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም በመጨመር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ወሳኝ ነው!›› 

አቶ ግርማው ፈረደ በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ

EED የካቲት 25/ 2017 ዓ.ም (ቢሾፍቱ)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ሀገር-አቀፍ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስትራቴጂ ዝግጅትን በተመለከተ ከፌዴራልና የክልል አስፈጻሚና ባለድርሻ አካላት ጋር በቢሾፍቱ ከተማ አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡

የውይይት መድረኩን የከፈቱት በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማው ፈረደ እንደገለፁት ተቋሙ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 526/2015 እንደ አዲስ ሲቋቋም ከተሰጡት ተግባርና ኃላፊነት ውስጥ አንዱ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት ነው፡፡

በዚህም የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም በመጨመር ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የሚረዳ ሀገር-አቀፍ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስትራቴጂ ለማዘጋጀት የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ፕሮጀክት አምራች ኢንተርፕራይዞች በፋይናንስ አቅርቦት፣ በአቅም ግንባታ እንዲሁም በንግድ ልማት አገልግሎት ያሉባቸውን ክፍተቶች በመሙላት አምራች ዘርፉ ባለው የመልማት ፀጋ ልክ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ወ/ሮ የመንዝወርቅ ግረፌ ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ ሀገር-አቀፍ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ስትራቴጂ ለማዘጋጀት ውል የወሰደው ኮንሱል አማካሪ ድርጅት ስትራቴጂውን ለማዘጋጀት እየተከናወኑና በቀጣይ የሚከናወኑ ስራዎችን አቅርቦ ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

News