
በአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፉ ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚና ተሳታፊ የሚያደርጉ ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተመላከተ
EED የካቲት 21/2017 ዓ.ም (አዳማ)
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በስርዓተ ፆታ ትንተናና ፆታ ተኮር ጥቃት ዙሪያ ለተቋሙና ለዘርፉ ለክልል የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአዳማ ከተማ እየሰጠ ነው።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በስልጠና መድረኩ እንደተናገሩት በአምራች ዘርፉ የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመው፤ በተለይም ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ፆታን ተኮር ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከል የሚያስችሉ ስራዎችን በእቅድ አካቶ መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮግራም ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ ላይ ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞችን ተገቢውን ድጋፍ አግኝተው በዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስርአተ ፆታ ላይ ያሉ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የተቋሙ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትዕግስት ድጋፌ በበኩላቸው እንደገለፁት ፃታን ተኮር ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር እንዲቻል የስርዓተ ፆታ ባለሙያዎች የተሻለ ግንዛቤ ይዘው ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ስልጠናው በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት አማካኝነት እየተሰጠ ይገኛል::
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት