ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

የኢትዮጵያ ታምርት 2017 ኤክስፖ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የገበያ ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ትስስር እንዲፈጥሩ አስችሏል!

አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

EED ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ታምርት 2017 ኤክስፖ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የገበያ ተጠቃሚ ከማድረግም ባለፈ ትስስር እንዲፈጥሩ አስችሏል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለፁት ኤክስፖው አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የገበያ ተጠቃሚ ከማድረግም ባለፈ ትስስር እንዲፈጥሩ በማስቻሉ ረገድ ውጤታማ ነበር::

ለሶስተኛው ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን ያስተዋወቁበት፣ ሰፊ ግብይት ያካሄዱበት፣ ዘላቂ የገበያ ትስስር የፈጠሩበት እንዲሁም ገንቢ ልምድና ተሞክሮ የተገኘበት እንደነበር ም/ዋና ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አምራች ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ ያሳየ መሆኑን የገለፁት አቶ አብዱልፈታ አምራች ኢንተርፕራይዞች ጥራት ያላቸውን ምርቶች በማምረት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ልማት መ/ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል::

በዝግጅቱ የተሳተፉ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በሰጡት አስተያየት በኤክስፖው መሳተፋቸው ምርቶቻቸውን ከማስተዋወቅና ግብይት ከማከናወን ባለፈ በተለይም አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘትና የተሻለ ልምድና ተሞክሮ ማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች የተሳተፉበት በመሆኑ አነስተኛና መካከለኛ አምራቾች ያሉበትን ደረጃ እንዲያዩ እንዳስቻላቸው ገልጸው በቀጣይ የምርቶቻቸውን ጥራት፣ አይነትና መጠን ማሳደግ የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንዳነሳሳቸውም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከሚያዝያ 25-29/2017 ዓ.ም በተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 100 የሚሆኑ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ተሳትፈዋል::

News