አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

“ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ምርታማነትና ተወዳዳሪነት የሰው ሐይልን ማብቃት ወሳኝ ነው!”
አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር
EED ሚያዝያ 08/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የበጀት ዓመቱ 9 ወራት እቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በአምራች ዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማሳተፍ ጥራት ያላቸው ምርቶችን ማምረትና መፍጠር ካልተቻለ በዘርፉ ተወዳዳሪ ለመሆን አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል::

ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ምርታማነትና ተወዳዳሪነት የሰው ሐይልን ማብቃት ወሳኝ መሆኑን የገለጽት ም/ዋና ዳይሬክተሩ የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ፕሮግራምን ውጤታማ ለማድረግ የሰለጠነ የሰው ሐይል ልማትን ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል::
አቶ አብዱልፈታ የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ፕሮግራም በገጠር በርካታ የስራ እድል ለመፍጠር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው የሰው ሃይልን ማብቃት፣ የፋይናንስ አቅርቦትን ወደታች ማውረድ፣ የማምረት አቅምን ማሳደግ የሚያስችሉ ድጋፎችን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ አሰራሮችን ለመዘርጋትና ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!