ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አቶ ጳውሎስ በርጋ ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

“መንግስት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለመደገፍ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው”

አቶ ጳውሎስ በርጋ ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

EED ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት በአዲስ ምርት መፈብረክ (New product development) በሚል ርዕስ ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ። 

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት ተኪ ምርት አምራቾችን በልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚደግፍ ገልፀዋል።

በተለይም የእንጨት፣ የብረታ ብረትና ማሽነሪ አምራች ኢንተርፕራይዞች በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገዙ ምርቶችን በመተካት ረገድ የጎላ ሚና እንዳላቸው አመላክተዋል።

በዚህም የአመራረት ሂደታቸውን ፈጠራ የታከለበት የምርት ስብጥር እንዲያሰፉ የሚረዳ ተከታታይ ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን በማዘጋጀት በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ጥራት ያለው ምርት ማቅረብ እንዲችሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል።

በተለይም መንግስት የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና እንዲሁም የአለም የንግድ ድርጅትን አባል በመሆን የገበያ አማራጮችን ለማስፋት እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ ጳውሎስ አምራች ኢንተርፕራይዞች ከዚህ ስልጠና ያገኙትን ተሞክሮ በግብአትነት በመጠቀም ከሀገር ውስጥ ገበያ ባሻገር  በአለም ገበያ ተወዳድሮ ማሸነፍ የሚችል ጥራት ያለው ምርት ለማቅረብ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።

በመጨረሻም ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል::

#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት

ለተጨማሪ መረጃ ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News