አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

‹‹በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ያደጉ ሀገራት ተሞክሮ የሚያሳየው ለዘርፍ እድገት ቀዳሚው ጉዳይ የበላይ አመራሩ ቁርጠኝነት ነው!››
አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር
EED መጋቢት 30/2017 ዓ.ም (ሆሳዕና)
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር እንደሻው ጣሰው በተገኙበት ከክልሉ የአምራች ዘርፉ አመራርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ባለሀብቶች ጋር በሆሳዕና ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በመድረኩ እንደተናገሩት በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ያደጉ እንደ ሲንጋፖርና ቬትናም የመሳሰሉ ሀገራት ልምድና ተሞክሮ የሚያሳየው ለዘርፍ እድገት ቀዳሚው ጉዳይ የበላይ አመራሩ ቁርጠኝነት ነው፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም ዘርፉን ለማሳደግ እያደረገ ያለውን ጥረት የሚደነቅ መሆኑንና ክልሉ የሰላም አየር የሰፈነበት፣ ቁርጠኛ አመራር ያለበትና ለአምራች ዘርፉ የተመቸ በመሆኑ ባለሀብቶች ያሉ እምቅ ሀብቶችንና የተመቻቹ እድሎችን በመጠቀም ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በገጠር የኢንዱስትሪ መንደርን ለመመስረት፣ በገጠር የሚገኝውን ጥሬ እቃና ከፍተኛ የሰው ሃይልን ወደ ስራ ለማስገባትና የአምራች ዘርፉን ለማሳደግ የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽንና ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በገጠር ኢንዱስትሪን ለማስፋፋት ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅርበት መስራት እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በገጠር ያለውን የቁጠባ አቅም የገጠር ኢንቨስትመንትን ለማበረታታትና አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ለማቋቋም ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ከልብ መደገፍ እንደሚገባ የገለጹት አቶ አብዱልፈታ የበለጸገ ሀገር ለመፍጠር በሚደርገው ጥረት አምራች ኢንዱስትሪን ማስፋፋትና ማሳደግ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!