ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

“ተወዳዳሪ አምራች ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር እንዲቻል በተሻለ እውቀትና አቅም መደገፍና መፈፀም ይኖርብናል!”

አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር

EED የካቲት 26/2017ዓ.ም (አዳማ)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት “የላቀ አቅም የላቀ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ተነሳሽነት፣ ለኢንተርፕራይዝ ልማት” በሚል መሪ ቃል አምራች ዘርፉን ለመደገፍ በተዘጋጅ ስትራቴጂዎች፣ መመሪያዎችና የአሰራር ስርዓቶች ላይ ለክልልና ከተማ አስተዳደር መካከለኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በአዳማ ከተማ እየሰጠ ነው።

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ የስልጠና መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን  በማስፋፋትና በማጠናከር ተኪ ምርትን ማስፋት፣ ኤክፖርትን ማሳደግና ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል ያስፈልጋል ብለዋል።

በተሻለ እውቀትና አቅም በመደገፍ ተወዳዳሪ አምራች ኢንተርፕራይዞች እንዲፈጠሩ መስራት ይገባል ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ዘርፉን የሚደግፈው አስፈፃሚ አካል የተሻለ  እውቀት፣ የላቀ ፈጠራ፣ፍጥነትና ተነሳሽነት እንዲሁም የጋራ ግንዛቤ ይዞ መፈፀም እንዲችል የአቅም ግንባታ  ስልጠናው መመቻቸቱን ተናግረዋል።

ስልጠናው ዘርፉን ለሚደግፉና ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ 171 ለሚሆኑ መካከለኛ አመራሮች እየተሰጠ ሲሆን የምርትና ምርታማነት ማሻሻል፣ ተኪ ምርት ስትራቴጂ፣ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ሽግግር ስትራቴጂና መመሪያ፣ የማምረት አቅም አጠቃቀም ልኬት፣ የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት የአሠራር ሥርዓትና ሌሎች የስልጠና ሰነዶች ላይ ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ 

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

News