
“ትልቁ ሀብት ያለው በገጠር በመሆኑ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ፕሮግራም መጀመር ሀገርን ሊያሳድግና ዜጎችን በስፋት ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል!”
በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት
EED ሚያዝያ 08/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በበጀት ዓመቱ 9 ወራት የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በግምገማ መድረኩ እንደገለፁት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች እንዲስፋፉና እንዲያድጉ ብሎም በዘርፉ የሚፈጠረው የስራ ዕድል እንዲሰፋ የተሰራው ስራ ጥሩ ቢሆንም ከዚህ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንዲቻል የዘርፉን ተግዳሮቶች በአግባቡ ለይቶ መፍታትና መደገፍ እንደሚገባ አመላክተዋል።
የቋሚ ኮሚቴ አባላት በገጠር ያለውን ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋልና ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሼቲቭ መጀመሩ አበረታች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ፕሮግራሙን በውጤታማነት መፈፀም እንዲቻል የመሰረተ ልማት፣ የፋይናንስ፣ የሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦትና ሌሎች ድጋፎች እንዲመቻቹ ከባለድርሻ አካላትና ከክልሎች ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እንደሚያስፈልግም የምክር ቤት አባላቱ ገልጸዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!