ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው

EED ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በመተባበር አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ተጠቃሚ ለማድረግ በተዘጋጀው ፕላትፎርም ዙርያ ለተቋማቱ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በመድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት አስተባባሪ ወ/ሮ የመንዝወርቅ ግረፌ ፕሮጀክቱ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተለያዩ ስራዎች መስራታቸውን ገልጸዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በሃገር አቀፍ ደረጃ ባለው የመዳረሻ ስፋትና የረጅም ጊዜ ልምድ አማካሪ ድርጅቶቹ የሚያለሙትን የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት በመጠቀም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ያመረቷቸውን ምርቶች ለተጠቃሚዎች በማድረስ ረገድ ውጤታማ ስራ እንደሚሰራ ስለታመነ ለዚህ ስራ መመረጡን አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳግማዊ ሀይልዬ በበኩላቸው እንደገለፁት የሚዘጋጀው የኤሌክትሮኒክስ ግብይት  ስርዓት አላማ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የሀገር ውስጥና ውጭ የገበያ መዳረሻና ዕድል ማስፋት እንደሆነ አብራርተዋል። 

በሀገራችን የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ጅማሮች ቢኖሩም ይህኛው ግን ድንበር ተሻጋሪ ንግዶችን በማቀላጠፍና ኢ-መደበኛ ንግዶችን በመመለስ በአጠቃላይ የሀገሪቱ ገቢ ላይ አውንታዊ ለውጥ የሚፈጥር በመሆኑ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የሀገሪቱን የግብይት ስርዓት አንድ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው አቶ ዳግማዊ አመላክተዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ፕላትፎርሙን ያዘጋጀው ሲ ኤስ ኤም አፍሪኮም የተባለ አማካሪ ድርጅት ሲሆን በኤሌክትሮኒክስ ግብይት የሚሸጡ ምርቶችን ለተጠቃሚዎች በማድረስ ረገድ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ነው።

በመድረኩ ስልጠናው በቀጣይ ለባለሙያዎችና አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት  #እኛም_እንሸምት

ተጨማሪ መረጃ፡-

#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et

#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment

#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment

#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise

#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com

News