ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የበጀት ዓመቱ 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ

​EED (ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም)

​

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የማኔጅመንት አባላት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የሪፎርም ስራዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

​

በማኔጅመንት አዳራሽ በተካሄደው ውይይት አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ከማቋቋምና ከማጠናከር አንፃር፣ ከስራ እድል ፈጠራ፣ ከተኪ ምርትና ወጪ ምርት ጋር በተያያዘ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

​

በተጨማሪም የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሺየቲቭ እቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

​የማኔጅመንት አባላቱ በሪፎርም ስራዎች ላይ የተወያዩ ሲሆን፣ የቀጣይ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል።

​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

​📌 ለተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይከተሉ፦

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

News