
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የበጀት ዓመቱ 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ
EED (ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የማኔጅመንት አባላት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የሪፎርም ስራዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በማኔጅመንት አዳራሽ በተካሄደው ውይይት አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ከማቋቋምና ከማጠናከር አንፃር፣ ከስራ እድል ፈጠራ፣ ከተኪ ምርትና ወጪ ምርት ጋር በተያያዘ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

በተጨማሪም የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሺየቲቭ እቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የማኔጅመንት አባላቱ በሪፎርም ስራዎች ላይ የተወያዩ ሲሆን፣ የቀጣይ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት
📌 ለተጨማሪ ወቅታዊ መረጃዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይከተሉ፦
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment