
የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የበጀት ዓመቱ እቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት መነሻ ዕቅድ ግምገማ መድረክ ተካሄደ
EED ሰኔ 20/ 2018 ዓ.ም
የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት መነሻ ዕቅድ የውይይት መድረክ ተካሄደ::

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ በመድረኩ የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የውይይቱ መሠረታዊ ዓላማ በበጀት አመቱ የተከናወኑ ተግባራትን ጥንካሬዎችና ያጋጠሙ ማነቆዎችን ለመገምገም መሆኑን ገልጸዋል።

በሥራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት በጋራ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችሉ ስልቶች ይቀመጣሉ ያሉት አቶ ጳውሎስ ይህም ተቋማዊ ግቦችን በብቃት ለማሳካት የሚያስችሉ ቁልፍ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ እንደሚረዳ ጠቁመዋል።

በመድረኩ የበጀት አመቱ የዕቅድ ክንውን ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷበታል። እንደ ሀገር በቀጣይ ዓመት ሊከናወኑ በታቀዱ ተግባራት እና አዳዲስ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ጥልቅ ምክክር ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የማኔጅመንት አባላት፣ የክልል የዘርፉ ቢሮዎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የእቅድ ባለሙያዎችና የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ኢንሼቲቭ አስተባባሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል::
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት
#ለተጨማሪ_መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ!
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment