ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ነባር የስራ ሂደት ፍሰት ጥናት ላይ ውይይት ተካሄደ

EED (ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት በብቃትና በእውቀት ላይ ተመስርቶ ለማዳረስ ያስችለው ዘንድ፣ የነባር የስራ ሂደት ፍሰት (AS-IS)  ጥናት ላይ ከማኔጅመንት አባላትና ከመካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ።

በተቋሙ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የምክክር መድረክ፣ ነባር የስራ ሂደት ፍሰት ዝርዝር ጥናት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

ጥናቱ የተካሄደበት ዋና ዓላማ የተቋሙን ዋና ዋና የሥራ ዘርፎች፣ የሥራ ሂደቶችና የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቶች በጥልቀት በመመርመር ወቅታዊ አሠራራቸውን በግልጽ መረዳት እንደሆነ ተገልጿል።

በተጨማሪም በሥራ ሂደቶች ውስጥ የሚታዩ  አሰራሮችን በዝርዝር በመለየት፣ ወደፊት የሚቀረጽን ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ውጤታማ የሥራ ሂደት (TO-BE) ለመዘርጋት የሚያስችል ጠንካራ መሠረት ለመጣል የተከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል።

በውይይቱ ላይ ከቡድን መሪዎች ጀምሮ ያሉ የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች የተሰጡ ገንቢ አስተያየቶችና ተጨማሪ ምክረ-ሃሳቦች በጥናቱ ላይ እንደ አስፈላጊ ግብዓት ተወስደው ጥናቱን የበለጠ የማዳበርና የማጠናከር ሥራ ይከናወናል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የኢንተርፕራይዞች ምርታማነት ለማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማፋጠን፣ የገበያ ትስስር ለመፍጠርና ተኪና ወጪ ምርት ለማሳደግ የሚሰጣቸውን ድጋፎች የተቀላጠፉና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የሪፎርም ሥራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል።

​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

ለወቅታዊ መረጃዎች የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይከታተሉ፦

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

News