የስልጠናው ተሳታፊ አምራች ኢንተርፕራይዞች

“ስልጠናው ተጨማሪ ክህሎት እንድናገኝ አስችሎናል!”
የስልጠናው ተሳታፊ አምራች ኢንተርፕራይዞች
EED ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም (አዳማ)
በአዲስ ምርት መፈብረክ (New product development) በሚል ርዕስ ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

አዲስ ምርት መፈብረክ ላይ የተሰጠው ስልጠና ከነበረን ዕውቀት ላይ ተጨማሪ ክህሎት እንድናገኝ አስችሎናል ሲሉ የስልጠናው ተሳታፊዎች ተናገሩ።

ስልጠናው ከመደበኛ ስራችን ጋር በቀጥታ የተሳሰረ በመሆኑ አዳዲስ ምርቶችን ሳይንሳዊ በሆነ ፤ በአጭር ጊዜ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዴት መፈብረክ ፣ ማምረትና ወደ ገበያ ማቅረብ እንደሚቻል ከስልጠናው እንደተማሩ ገልፀዋል።

ለ6 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ እንደነበር የገለፁት የስልጠናው ተሳታፊዎች ከመደበኛ ስልጠናው ባሻገር መድረኩን እርስ በርስ ትስስር ለመፍጠርና ልምድ ለመለዋወጥ እንደተጠቀሙበት ገልፀዋል።
ስልጠናውን በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ከኮንሱል አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር መስጠት ተችሏል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት
ለተጨማሪ መረጃ ፡-
#ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et
#ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/Ethiopianenterprisedevelopment
#ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevelopment
#ዩትዩብ፡ https://youtube.com/@ethiopiaenterprise
#ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com