ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ለ151,726 ዜጎች አዲስ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል!

አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

EED ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የ2017 በጀት ዓመት 9 ወራት እቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለፁት፣ በበጀት ዓመቱ 9 ወራት አዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋምና ነባሮቹን በማጠናከር ለ151,726 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 2,752 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም እንደተቻለ የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ 979 አምራች ኢንተርፕራይዞች ከአነስተኛ ወደ መካከለኝ እንዲሁም 33 አምራች ኢንተርፕራይዞች ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ በድምሩ 1,012 አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማሸጋገር ተችሏል ብለዋል፡፡

ም/ዋና ዳይሬክተሩ ለ14,183 አምራች ኢንተርፕራይዞች ችግራቸውን መሰረት ያደረገ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት እንደተቻለና ለ1,209 አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ከ6 ቢልየን ብር በላይ የስራ ማስኬጃ ብድር እንዲሁም ለ889 ኢንተርፕራይዞች ከ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ማሽኖችን በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት አማካኝነት ማቅረብ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

አቶ አብዱልፈታ አክለውም 1,451 ተኪ ምርት የሚያመርቱ ኢንተርፕራይዞች 902,191 ቶን ተኪ ምርት ማምረት እንዲችሉ በመደገፍ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን እንደተቻለም አያይዘው ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!

News