ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

“አምራች ዘርፉ መሰረታዊ ለውጥ እንዲያመጣ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው!”
ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር
EED ሚያዚያ 1/2017 ዓ.ም (ሆሳዕና)
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር እንደሻው ጣሰውና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከአምራች ዘርፉ አመራር፣ ባለድርሻ አካላትና ባለሀብቶች ጋር በሆሳዕና ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ እንዲያድግና መሰረታዊ ለውጥ እንዲያመጣ የሚያስችሉ ስራዎች በትኩረት እየተሰራ ነው::
የገበያና የግብዓት ትስስር፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ስትራቴጂና የክላስተር ልማትን በግልና በመንግስት አጋርነት ለማልማት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ጥናት በአማካሪ ድርጅቶች በኩል እየተዘጋጁ መሆኑን ገልፀዋል::

ለአምራች ዘርፍ የረዥም ጊዜ መደላድል እየተፈጠረ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ በተለይም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ ከዘርፉ ባለድርሻ ተቋማት ጋር ተቀራርቦ መስራትና ችግሮችን እየለዮ መፍትሄ መስጠት እየተቻለ መሆኑን ተናግረዋል::
ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራራቸውን እንዲያጠናክሩ፣ በዕቅድ የሚመራና ችግር የሚፈታና እንዲሆን ማድረግ እንደሚያስፈልግም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል::
ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽን በሀገር ውስጥ እየተመረተ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር አለባቸው ይህም በዘርፉ ለተሰማሩና መሰማራት ለሚፈልጉ ኢንተርፕራይዞች ትልቅ እድል መሆኑን ተናግረዋል::
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!