ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

የተከበሩ ዶ/ር እንደሻው ጣሰው፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር

“አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ለወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ፈጠራና ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት መሰረት ናቸው!”

የተከበሩ ዶ/ር እንደሻው ጣሰው፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር

EED መጋቢት 29/2017 ዓ.ም  (ሆሳዕና)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአምራች ዘርፉ አመራርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ባለሀብቶች ጋር በሆሳዕና ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡ 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር እንደሻው ጣሰው በመድረኩ እንደተናገሩት አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ለወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ፈጠራና ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት መሰረት ናቸው፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ የሚሰሩ እጆችን ማስፋፋትና ማበረታታት እንደሚያስፈልግ ገልጸው በተለይም ገጠር ላይ ኢንዱስትሪን በማስፋፋት የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽንና ትራንስፎርሜሽንን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት ለመቀነስ የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽንን ማስፋፋት እንደሚገባ የጠቁሙት ዶ/ር እንደሻው የስራ እደል ፈጠራ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን መጠቀም፣ ተኪ ምርትና ወጪ ምርትን ማስፋፋት የክልሉ የትኩረት አቅጣጫም እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

በአምራች ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀታቸው የገለጹት ርዕሰ መስተዳደሩ ባለሀብቶች ወደ አምራች ዘርፉ እንዲገቡና ውጤታማ እንዲሆኑ ባለድርሻ አካላት የጀመሩትን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ ወደአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ አዲስ ለሚገቡ ባለሀብቶች ያሉ ሀገራዊና ክልላዊ ምቹ ሁኔታዎች፣  ከመንደር ወደሀገር፣ በኢንዱስትሪ መሻገር-የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ትራንስፎርሜሽን በኢትዮጵያ እና የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት አፈጻጸም ቀርበው ውይይት ተካሂዷባቸዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊ ባለሀብቶች ከመሰረተ ልማት፣ ግብዓትና ፋይናንስ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ያጋጠሟቸውን ችግሮች አንስተው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቷበታል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!

News