ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

“አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ እንዲሆኑ ባለፉት 9 ወራት በተደረገው ድጋፍ የተሻለ አፈፃፀምና ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል!”

ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር

EED ሚያዝያ 08/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የበጀት ዓመቱ 9 ወራት እቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣  ከዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር  በአዳማ ከተማ እየገመገመ ነው።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ  በመድረኩ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ 9 ወራት አምራች ኢንተርፕራይዞች ችግሮቻቸው እንዲፈቱና እንዲጠናከሩ በተሰጠው ድጋፍ ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም መመዝገቡን እንዲሁም አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን ከማቋቋም አንጻር 76 በመቶ ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል።

ነባሮችን በማጠናከርና አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋም ከዕቅድ በላይ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም ገልፀው ለዚህ ውጤት መመዝገብ ከባለድርሻ አካላትና ከክልሎች ጋር ተቀራርቦ መስራት በመቻሉ እንደሆነም አመላክተዋል።

አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ውጤታማ እንዲሆኑ በፋይናንስና በግብዓት አቅርቦት፣ በገበያ ትስስር፣  በስልጠና፣ በመሰረተ ልማትና በመሰል ድጋፎች እንዲደገፉና እንዲጠናከሩ ሰፊ ስራ መሰራቱም ተናግረዋል።

በቀጣይ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ አሰባሰብና አስተዳደር እንዲኖር፣ የተሻለና ውጤታማ የክትትልና ድጋፍ ስራዎች እንዲሰሩ በትኩረት የሚሰራበት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢንሼቲቭን በተመለከተ ለክልል አመራሮች፣ ለባለድርሻ አካላት፣ ዘርፉን ለሚደግፉ ባለሙያዎች፣ ለሚዲያ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራቱን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ  ፕሮግራሙ ከተጀመረ  205 አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ምንም ኢንዱስትሪ በሌለባቸው የገጠር ወረዳዎች በማቋቋም ለ1 ሺህ 525 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል።

የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በመድረኩ የፌዴራል መንግስት የ9 ወራት  አጠቃላይ አፈፃፀምና ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ መግለጫን በተመለከተ ያቀረቡ ሲሆን የተቋሙ የ9 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ኢንሺየቲቭም ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት ይገኛል፡፡

‎#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!

News