ETHIOPIAN ENTERPRISES DEVELOPMENT

Empowering Manufacturing SMEs for National Economic Transformation and Societal Prosperity !

አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

‹‹የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ኢንሺየቲቭን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ጥራት ያላቸው ሞዴል ቢዝነስ ፕላኖችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል!››

አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

•  ሞዴል ቢዝነስ ፕላኖችን ለሚያዘጋጁ የተቋሙ ባለሙያዎች በኢንሺየቲቩ ዙርያ ገለጻ ተደርጓል::

EED መጋቢት 8/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ኢንሺየቲቭን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ጥራት ያላቸው ሞዴል ቢዝነስ ፕላኖች እንዲዘጋጅ በትኩረት እየሰራ ነው፡፡

በገጠር አምራች ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም ቢዝነስ ፕላኖችን ከሚያዘጋጁ የተቋሙ ባለሙያዎች ጋር በኢንሺየቲቩ ዙርያ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የልማት መ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ኢንሺቲቭ የአካባቢን ፀጋ እሴት በመጨመር ወደምርት መቀየርና በርካታ የስራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን በአካባቢ የሚገኝ ጥሬ ዕቃ፣ እውቀት/ችሎታ እና ጉልበትን በመጠቀም ለገጠር ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ ኢንዱስትሪዎችን ለመፍጠር እንደሚግዝ የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ኢንሺየቲቩ ለሀገራችን አዲስ ቢሆንም በሌሎች ሀገራት ውጤት የተገኘበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ኢንሺየቲቭን ውጤታማ ለማድረግ ጥራት ያላቸው ቢዝነስ ፕላኖችን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በየክልሉ ያሉ ጸጋዎችን ታሳቢ ያደረገ ሳይንሳዊ ሞዴል ቢዝነስ ፕላኖች ማዘጋጀት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡

ፕሮግራሙ በሁሉም የገጠር ወረዳዎች የአካባቢውን ፀጋ መሰረት በማድረግ የተሻለ መሠረተ ልማትና  አቅም ባላቸው ወረዳዎች ሦስት፣ መካከለኛ መሠረተ ልማትና አቅም ባላቸው ወረዳዎች ሁለት እንዲሁም ዝቅተኛ መሠረተ ልማትና አቅም ባላቸው ወረዳዎች ቢያንስ አንድ አነስተኛ ወይም መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም ይሰራል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

News