“እንደ ሀገር የተጀመሩ ሪፎርሞች ለአምራች ኢንዱስትሪ ዕድገት ሚናቸው የጎላ ነው” አቶ መላኩ አለበል

የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ጋር የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደተናገሩት እንደ ሀገር የተጀመሩ ሪፎርሞች ለአምራች ኢንዱስትሪ ዕድገት ሚናቸው የጎላ ነው ብለዎል። በተለይ በቅርቡ የተደረገው የኢኮኖሚ ሪፍርም ለአምራች ኢንዱስትሪ የወጪ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገር ውስጥ ለመሳብ፣ የወጪ ንግድና የማምረት አቅም አጠቃቀም ለማሳደግ ያለው ድርሻ […]

በ2016 በጀት አመት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ከ7.2 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ተሠራጭቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በ2016 በጀት አመት ለ2,573 አምራች ኢንተርፕራይዞች ስራ ማስኬጃና የማምረቻ መሳሪያ አቅርቦት 7.27 ቢልዮን ብር እንዲቀርብ ማድረግ መቻሉን የተቋሙ የስራ አመራር ስራ አስኪያጅ አቶ ከላሊ ወ/ገብርኤል ገለፁ። የፋይናንስ አቅርቦት ስርጭቱ በ2.839 ቢልዮን ብር የ1,634 አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን የስራ ማስኬጃ ብድር አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ታቅዶ 83% ለሚሆኑት 1,352 አምራች ኢንተርፕራይዞች 2.999 ቢሊዮን ብር […]

ተቋሙ የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀምን ገመገመ

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራሮችና ሰራተኞች የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም ላይ ናቸው፡፡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ በግምገማ መድረኩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር መድረኩ የተጠናቀቀውን በጀት አመት አፈፃፀም ገምግመን የተጀመሩ ውጤታማ ስራዎችን ለመጪው አመት በማሻገር የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በትጋትና በበለጠ ተነሳሽነት ስራችንን ለመቀጠል የምንመካከርበት ነው ብለዋል ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ በዚሁ መልዕክታቸው ስራችን ሰፊ፣ […]

ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን አዎንታዊ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅናና ሽልማት ተሰጠ

በየተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገትና ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱ የአምራች ኢንዱስትሪ ኩባንያዎችና ተቋማት እውቅናና ሽልማት ተሰጠ በተለያዩ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎች በመሰማራት የሀገር ውስጥ ግብዓት በመጠቀም የእሴት ጭማሬ ምጣኔ፣ የተሰማሩበት የአምራች ኢንዱስትሪ ብዛት እና በሌሎች መመዘኛ መስፈርቶች ለሀገር ኢኮኖሚ ላቅ ያለ አበርክቶ ያላቸው 22 የአምራች ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እውቅናና […]