የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከዩኒዶ ግሎባል ማርኬት አክሰስ ፕሮግራም ጋር በማር ማቀነባበር የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሄደ

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከዩኒዶ ግሎባል ማርኬት አክሰስ ፕሮግራም ጋር በማር ማቀነባበር የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሄደ EED (ህዳር 27/2017 ዓ.ም) የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ከዩኒዶ ግሎባል ማርኬት አክሰስ ፕሮግራም ከመጡ ልዑካን ጋር በማር ማቀነባበር የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን ችግሮች መፍታት የሚያስችል ድጋፍ በሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡ ም/ዋና ዳይሬክተሩ በውይይቱ ላይ […]

ሀገር አቀፍ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ባዛር ሊካሄድ ነው

“የኛ ምርት፣ ለእኛ” የአምራች ኢንተርፕራይዞች ባዛር ! የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከጆርካ ኤቨንትስ ጋር በመተባበር ከታህሳስ 18-27/2017ዓ.ም በአዲስ አበባ ፍልውሃ አካባቢ በሚገኘው ፊንፊኔ ሆቴል አጠገብ የሚካሄድ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ባዛር አዘጋጅቷል፡፡ “የኛ ምርት፣ ለእኛ” የአምራች ኢንተርፕራይዞች ባዛር! በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ #ሀገር_አቀፍ ባዛር በአልባሳትና የቆዳ ውጤቶች፣ በእንጨትና ብረታብረት ውጤቶች፣ በአግሮፕሮሰሲንግ፣ በኬሜካልና ኬሜካል ውጤቶች፣ […]

የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች በአንድ ጀንበር 600 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አመራርና ሰራተኞች በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ስኬት አስተዋፅኦ ለማድረግ በICT Park ቅጥር ግቢ በመገኘት ችግኞችን ተከሉ። በመርሐ-ግብሩ የደን ሽፋንን የሚያሳድጉ፣ ለአካባቢ ጥበቃ አስተዋጽኦ የሚያደርጉና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል። በዚህም ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን በተለይ ለምግብነት የሚውሉ እና ለሌማት ትሩፋት ስኬታማነት አበርክቶ እንዲኖራቸው በልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ችግኞቹ […]

በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነነት ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተጠቆመ

EED ነሃሴ 19/2016 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከክልልና፣ ከተማ አስተዳደር፣ ተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጻምና የ2017 ዕቅድን እየገመገመ ነው። በመድረኩ የተሳተፉት የዘርፉ አመራሮች እንደተናገሩት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደቻሉ ገልጸዋል። ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀትና የሚያደርጋቸውን ድጋፍና ክትትል በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንዳለባቸው ጠቁመዋል። […]

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በ2016 በጀት ዓመት በሳየው የላቀ አፈፃፀም አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነ

EED ነሃሴ 19/2016 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የክልል፣ ከተማ አሰተዳደርና የተጠሪ ተቋማት በ2016 በጀት ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም ላመጡ ቢሮዎችና ተጠሪ ተቋማት እውቅናና ሽልማት አካሂዷል። የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር  ካሉ ተጠሪ ተቋማት በተጠናቀቀው በጀት አመት በዕቅድ አፈፃፀምና በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ስራዎች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆኗል። ተቋሙ የሀገር ውስጥ አምራቾች ምቹ የቢዝነስ ከባቢ እንዲፈጠርላቸውና […]

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ለድሬዳዋ አስተዳደር ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን በተቋማዊ መዋቅርና አደረጃጀት ዙርያ ተሞክሮውን አጋራ

EED (መስከረም 09/01/2017ዓ.ም) የተሞክሮ ልውውጡን የመሩት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ የአምራች ኢንተርፕራይዞች ዋነኛ ማነቆ የሆነውን የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ችግር በክላስተር ኮርፖሬሽን ለመፍታት የድሬዳዋ አስተዳደር የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ክላስተር ኮርፖሬሽን አቋቁሞ እየሰራ መሆኑ ለሌሎችም ክልሎችም ተሞክሮ መሆን የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አምራች ኢንተርፕራይዞች የክላስተር መሰረተ ልማት እንዲሟላላቸው ተቋሙ ከባለድረሻ አካላት ጋር በቅንጅት […]

“በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ106 ሚሊየን ዶላር በላይ የማሽነሪ ሊዝና የስራ ማስኬጃ ብድርን በማመቻቸት 1ሺህ 565 ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል”

ወ/ሮ የመንዝወርቅ ግረፌ ፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ፕሮጀክት አስተባባሪ በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ ፕሮጀክት በ2016 በጀት ዓመት 1ሺህ 565 አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በሊዝ ፋይናንስና በስራ መስኬጃ ብድር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የፕሮጀክቱ አሰተባባሪ ወ/ሮ የመንዝወርቅ ግረፌ ተናገሩ። ከዓለም ባንክ በተገኘው የብድር ድጋፍ ከ106 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ በኢትዮጵያ ልማት […]

በኢትዮጵያ እና በቻይና አቻ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል የሁለትዮሽ ውይይት ተካሄደ።

የውይይቱ ዋና ዓላማ በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ያጠነጠ ሲሆን በዚህም ከሁለቱም ሃገራት የተውጣጡና አቅም ያላቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ማህበረሰብ የልምድ ልውውጥ የሚያድረጉበት ስምምነት ላይ ተደርሷል። በኢትዮጵያ እና በቻይና አቻ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል በተደረገው የሁለትዮሽ ውይይት ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ተገኝተዋል፡፡ በልምድ ልውውጡ የቻይና አምራች ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም እና […]

የኢትዮጵያና ቻይና አምራች ኢንዱስትሪዎች ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ እዲዘጋጅ ስምምነት ላይ ተደረሰ

ከኢትዮጵያና ቻይና የተወጣጡና አቅም ያላቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ማኅበረሰቦች ልምድ የሚለዋወጡበት መድረክ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡ በኢትዮጵያና ቻይና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴሮች መካከል የሀገራቱን ንግድና ኢንቨስትመንት ለማጠናከር ያለመ ምክክር ተደርጓል፡፡ በውይይቱ ላይም ከሁለቱ ሀገራት የተወጣጡና አቅም ያላቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ማኅበረሰቦች የልምድ ልውውጥ የሚያድረጉበት መድረክ እዲዘጋጅ ስምምነት ላይ ተደርሷል። የልምድ ልውውጡ የቻይና አምራች ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም፣ ምቹ […]

“ኢትዮጵያ በአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማት እያደረገችው ያለው እንቅስቃሴ አስደናቂ ነው” የቼክ ሪፐብሊክ የቢዝነስ ልኡካን ቡድን

የቼክ ሪፐብሊክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ማህበርና የቼክ ኢንቨስት የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት እየተከናወኑ በሚገኙ እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ ከተቋሙ አመራሮች ጋር ተወያዩ። የልኡካን ቡድኑን የተቀበሉት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ እንደገለፁት በኢትዮጵያ ሠፊ የኢንዱስትሪ መሠረትን ለመጣል፣ የስራ ዕድል ለመፍጠርና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን ዕውን ለማድረግ የአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማትን እንደዋንኛ ስልት በመውሠድ ሠፊ […]